በህንድ ምዕራባዊ የባህር ጠረፍ ዳርቻ ላይ አንድ ሰው አልባ አውሮፕላን፣ ዛሬ ቅዳሜ ከእስራኤል ጋር ግንኙነት እንዳለው የተነገረለትን አንድ የንግድ መርከብ መትቷል ሲል አምበሬ የተባለው የብሪታንያ የባህር ላይ ደህንነት ድርጅት ተናግሯል።
ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ህንድ ይጓዝ በነበረና የላይቤሪያ ባንዲራ ባውለበለበው የኬሚካል ምርቶች ጫኝ መርከብ ላይ የእሳት ቃጠሎ መድረሱን ድርጅቱ አስታውቋል።
የህንድ የባህር ኃይል ባለስልጣን ለሮይተርስ እንደተናገሩት ቅዳሜ ጠዋት ለቀረበላቸው የእርዳታ ጥያቄ ምላሽ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡
“የመርከቧ ሠራተኞችና እና የመርከቧ ደህንነት መረጋገጡንም” ባለሥልጣኑ አስታውቀዋል፡፡
“የባህር ኃይሉ ወደ አካባቢው የተላከው የጦር መርከብም ከስፍራው ደርሷል፣ በሚፈለገው መጠንን እገዛ ያደርጋል›› ያሉት ባለሥልጣኑ፣ ስለ ጉዳዩ የመናገር ፍቃድ ስለሌላቸው ስማቸው እንዲጠቀስ ፍቃደኛ አልሆኑም።
እኤአ ጥቅም 7 ሃማስ በእስራኤል ላይ ከደረሰው የሽብር ጥቃት ተከትሎ እስራኤል ጋዛን ማጥቃት ከጀመረቸበት ጊዜ አንስቶ ፣ በኢራን የሚደገፉ ሁቲዎች በቀይ ባህር ላይ ባሉ መርከቦች ላይ የሚያደርሷቸውን የሰው አልባ በራሪዎች (ድሮኖች) እና የሚሳኤል ጥቃቶች እየተበራከቱ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
ለጥቃቱ እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ የለም፡፡