በዐማራ ክልል የተስፋፋው ግጭት፣ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ የደረሰው፣ ለግጭት የሚዳርጉ ችግሮች በአፋጣኝ ባለመፈታታቸው ነው፤ ሲል የሰላም ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ሚኒስቴሩ፣ የሩብ ዓመት አፈጻጸሙን፣ ዛሬ ዐርብ፣ ለተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት፣ በዐማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉ ግጭቶች ሥራውን እየተገዳደሩበት እንደኾነ አመልክቷል፡፡
ከሪፖርቱ በኋላ የምክር ቤቱ አባላት ላነሧቸው ጥያቄዎች፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሓላፊዎች መልስ በሚሰጡበት ወቅት፣ የብዙኀን መገናኛዎች እንዲወጡ ተደርጓል፡፡
ኾኖም፣ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደኣ፣ ከጋዜጠኞች ጋራ በነበራቸው አጭር ቆይታ፣ ሚኒስቴሩ፣ በዐማራ ክልል ግጭት ሊያስከትል የሚችል ኹኔታ በመኖሩ እልባት እንዲሰጠው ቅድመ ማስጠንቀቂያ አቅርቦ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።