“የተለያዩ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ማኅበረሰብ አባላት ለዘንድሮው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለውሳኔያቸው ምን ዓይነት ጉዳዮችን መሰረት ያደርጉ ይሆን?” ችችችችበሚል ላነሳነው ጥያቄ፣ ማብራሪያ እንዲሰጡን የአሜሪካ-ኢትዮጵያውያን የሕዝብ ጉዳዮች ኮሚቴ (ኤፓክ) ዋና ጸሐፊ አቶ ዮም ፍሰሃን ጋብዘናል።
ከተቋቋመ ሦስት ዓመት ተኩል የሆነው ኤፓክ፣ ሁለቱ ዕጩዎች በየበኩላቸው ከላኳቸው አራት የምርጫ ዘመቻ ተወካዮች ጋራ አባሎቻቸው ውይይት እንዲያደርጉ በቅርቡ መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። አቶ ዮም ማኅበራቸው ስላሰናዳው ስለዚህ መድረክም አስረድተውናል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።