በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ኮሬ ዞን፣ ጎርካ ወረዳ፣ ከረዳ እና ዳኖ ቀበሌዎች፣ ባለፈው እሁድና ሰኞ ጠዋት በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት አምስት ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ ነዋሪዎችና የተጎጂ ቤተሰቦች ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቁ።
የዞኑ የሰላም እና የፀጥታ መምሪያም የሰዎቹን መገደል ለአሜሪካ ድምፅ አረጋግጦ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎችን ተጠያቂ አድርጓል።
ከአካባቢው የተመረጡ የሕዝብ ተወካዮች በበኩላቸው መንግሥት በኮሬ ዞን የቀጠለውን ጥቃት እንዲያስቆም ጥሪ አቅርበዋል ።
ከጥቃቱ ጋር ስሙ ከተነሳው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከዚህ በፊት ለተመሳሳይ ውንጀላ በሰጠው ምላሽ ታጣቂዎቹ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ እንደማያደርጉ በመግለፅ ውንጀላውን አስተባብሏል።