በሱዳን ያለውን የእርስ በእርስ ጦርነት ለማስቆም የሚደረጉ አለም አቀፍ ጥረቶች ቢቀጥሉም እስካሁን ውጤታማ አልሆኑም፡፡
በሲውዘርላንድ በተካሄደው ውይይት ላይ ልዑካኖቹን ያልላከው የሱዳን ወታደራዊ መንግስት በካይሮ ከግብጽ እና አሜሪካ ሃላፊዎች ጋር እንዲወያዩ ልዑካኖቹን ለመላክ መስማማቱን አስታውቋል፡፡
በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ እና እስያ ጥናት እና ምርምር ማዕከል ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ሳሙኤል ተፈራ በሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች በኩል የተሰለፉ የውጭ ሃይሎች ፍላጎት መራራቅ ለድርድሩ አለመሳካት አንዱ ምክንያት ስለመሆኑ ይናገራሉ፡፡
ሱዳን የምትገኝበት የአፍሪካ ቀንድ በተራዘሙ ጦርነቶች፣ ትጥቅ ትግልና ሽብርተኝነት እየተፈተነ መሆኑን የሚገልጹት ዶክተር ሳሙኤል ተፈራ የዚህ ጦርነት መቋጫ በተሎ አለመገኘትም የቀጣናውን ችግር ያባብሳል ይላሉ፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ይከታተሉ፡፡