የጃፓኑ የፉኩሺማ ዳይቺ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ውድመት ከደረሰበት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ2011ዓ.ም. ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ጉዳት ከደረሰባቸው ከሦስቱ የኒውክሌር ኃይል መቀመሚያዎቹ የተበተኑ ፍርስራሾችን እና የኒውክሌር ቅልጥላጮችን በሩቅ በሚቆጣጠረው ሮቦት አማካኝነት ሊያስወግድ ያቀደበትን መንገድ የድርጅቱ አስተዳደር ዛሬ አሳየ።
አጉልቶ የሚያሳይ እና የሚመዘዙ ቱቦ መሰል መሳሪያዎች ያሉት ሮቦት በማሰማራት ከፉኩሺማ ዳይቺ ቁጥር ሁለት የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ አቅራቢያ ወዳድቆ የሚገኘውን የኒዩክሌር ፍርስራሽ ለማውጣት ለፊታችን ጥቅምት ዕቅድ መያዙን ነው የቶኪዮው የኤሌክትሪክ ኃይል ኩባንያ ይፋ አድርጓል።
ሥራው ሊጠናቀቅ ከታቀደለት ጊዜ ከሁለት ዓመት በላይ መዘግየቱም ተዘግቧል። የኒዩክሌር ቅልጥላጩን የማስወገዱ ሥራ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2021 ዓ.ም መገባደጃ ይጀመራል ተብሎ ቢታቀድም፤ በሬክታር ስሌት 9 ነጥብ ከተለካው፣ በ2011 አካባቢውን ከመታው ርዕደ መሬት እና ካስከተለው ሱናሚ ለማገገም የተሠራው ሥራ ሳቢያ መዘግየቱ ተጠቁሟል። ሮቦቱ ከተሰራባት ከምእራብ ጃፓኗ ኮቤ በሚገኘው የሚትሱቢሺ የከባድ ኢንዱስትሪዎች የመርከብ
መገጣጠሚያ ጣቢያ በተካሄደው የሙከራ ማሳያ ሂደት ሁለት እጅ መሰል ማንሻዎች የተገጠሙለት ሮቦት በዝግታ ወርዶ ጥቃቅን ፍርስራሾችን ሲያነሳ አሳይቷል።
ቴፕኮ በያዝነው የአውሮፓውያኑ 2024 መጀመሪያ ላይ ሮቦቶች ሊደርሱባቸው ካልቻሉ የፉኩሺማ ቁጥር 1 የኒውክሌር ማመንጫ ከሚገኘው የኒዩክሌር ፍርስራሹ ወደ ሌላ ሥፍራ እንዳይሰራጭ ከተቀመጠው መርከብ አቅራቢያ ያለውን ምስል እንዲቀርጹ አራት አነስተኛ ሰው አልባ በራሪ አካላትን ማሰማራቱ ተዘግቧል።