የተያዘው የአውሮፓውያኑ ግንቦት ወር፣ ለዓለም የአእምሮ ጤና ግንዛቤን ለማስጨበጥ የተመረጠ ወር ነው።
ይህንም ምክንያት በማድረግ በተሰናዳው “ሐኪምዎን ይጠይቁ” ውይይት፣ በዓለም ዙሪያ የሚታዩ ምስቅልቅሎች፣ ለአእምሮ ጤና ሁከቶች ማሻቀብና ለሕመሞች መባባስ ተጨማሪ መንሥኤ እንደኾኑ ባለሞያዎች ገልፀዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች፥ ዶክተር ተሾመ ሽብሬ፤ የአእምሮ ሐኪም እንዲሁም በካናዳው የዳልሃውሲ ዩኒቨርሲቲ የአእምሮ ሕክምና መምህር እና ተመራማሪ ናቸው፡፡ ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ ገዳ ደግሞ የነርቭ እና የአእምሮ ሐኪም፣ እንዲሁም በባሮ የነርቭ ሕክምና ተቋም መምህር እና ተመራማሪ ናቸው።
የውይይቱን የመጀመሪያ ክፍል ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።