የዶናልድ ትረምፕ በድጋሚ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ኾነው መመረጣቸው እንዳስገረማቸው በርካታ የውጭ ሀገር ምሁራን ተናገሩ። “የአሜሪካ መራጮችንና ትልቅ ቦታ የሚሰጧቸውን ጉዳዮች በውል አልተረዳንም ነበር” የሚል ስሜት እንዲሰማቸው ማድረጉንም አመልክተዋል።
ተመራጩ ፕሬዝደንት በሚቀጥለው አስተዳደራቸው ምን ዓይነት የውጭ ፖሊሲ እንደሚከተሉ እስካሁን በብዛት በግልጽ ባይታወቅም ጉዳዩን የሚከታተሉ አንድ ኢትዮጵያዊ ተንታኝ ተመራጩ ፕሬዝደንት ከተለመደው ወጣ ያለውን የውጭ ፖሊሲ አካሄዳቸውን “አሁንም ይቀጥላሉ” ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል ።
ትረምፕ የዓለም አቀፍ ፖለቲካ አካሄዳቸው በሁለትዮሽ ግንኙነቶች ላይ የተመሰረተ እንደሚኾን የገለጹ ተንታኞች በተለይም የአፍሪካ ቀንድን በሚመለከት የሚከተሉት መንገድ የአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅምን በማስጠበቅ ላይ የተቃኘ እንደሚሆን ይናገራሉ፡፡
የሐዋሳው ዘጋቢያችን ዮናታን ዘብዴዎስ እና የቪኦኤ ዋይት ሃውስ ዘጋቢ ፖትሲ ውዳኩስዋራን ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።