በዩክሬን ካርኺቭ ከተማ በሚገኝ የመኖሪያ ሰፈር ላይ የሩስያ በፈጸመችው ጥቃት 21 ሰዎች መቁሰላቸውን የካርኺቭ ርዕሰ መስተዳድር ዛሬ እሁድ አስታወቁ።
ርዕሰ መስተዳደሩ ኦሌግ ሳይንጉቦቭ በቴሌግራም ባስተላለፉት መልዕክት ስምንቱ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች ሆስፒታል ይገኛሉ ያሉ ሲሆን፤ ሁለቱ ደግሞ በጽኑ ህሙማን ክፍል እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
በሩሲያ የተፈጸመው ጥቃት በሲቪሎች መኖሪያ ላይ ሰዎች ተኝተው ሳሉ መፈጸሙ ተገልጿል።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በበኩላቸው ጥቃቱ ለምን ኃይሎቻቸው በምዕራባውያን አጋሮች የተሰጡ መሳሪያዎችን ተጠቅመው ወደ ሩሲያ ግዛት ጠልቀው በመግባት ማጥቃት እንዳለበቸው ያመላከተ ነው ቢሉም ፣ እስካሁን ድረስ ፈቃደኛ አልሆኑም።