በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ባወጡት መግለጫ፣ “ጉባኤ ያካሄደው ቡድን መንፈንቅለ መንግስት ለማካሄድ እየተንቀሳቀሰ ነው” ሲሉ ወንጅሉ፡፡
ትላንት፣ “የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት” በሚል ስም መግለጫ ያወጡት እነ አቶ ጌታቸው፣ የክልሉን የመንግስት መዋቅር ለማፍረስ ጥረት እያደረጉ ናቸው በማለት ጉባኤ ያካሄዱትን የህወሓት አመራሮች ከሰዋል፡፡
“እኛ ፓርቲ ነን” ያሉት፣ በአወዛጋቢው የህወሓት ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ሆኖው የተመረጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ፣ “ለግለሰቦች መግለጫ መልስ አንሰጥም” ሲሉ በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ አስተያየት እንደማይሰጡ ለአሜሪካ ድምፅ ጠቁመዋል።