‘ፍራንሲን’ በሚል የተሰየመችው ነፋስ የቀላቀለች አውሎ ነፋስ በአሜሪካ ሉዊዚያና ግዛት በሰፊው የኤሌክትሪክ የኃይል አቅርቦት እንዲቋረጥ ስታደርግ፣ በባሕር ዳርቻው አካባቢ የሚገኙ አካባቢዎች ላይ አደገኛ ዝናብና ነፋስ አስከትላለች፡፡
ሆኖም ግን ወደ ሚሲሲፒ ግዛት እየተቃረበች ስትመጣ ኃይሏ እየቀነሰ እንደመጣ የአሜሪካው ብሔራዊ የአውሎ ነፋስ መከታተያ ማዕከል አስታውቋል።
ፍራንሲን ትላንት ምሽት ሉዊዚያና ላይ ስታርፍ ፍጥነቷ 100 ማይል በሰዓት ነበር። በኒው ኦርለንስ የሚገኙትን ጨምሮ በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የኤሌክትሪ ኃይል ተቋርጦባቸዋል።
በሚሲሲፒ፣ አርካንሶ፣ ቴነሲ፣ አላባማ፣ ጆርጂያ እና ፍሎሪዳ ከባድ ዝናብ እንዲሁም ድንገተኛ ጎርፍ ሊከሰት እንደሚችል የአየር ሁኔታ ትንበያ ያመለክታል።