ኢትዮጵያና ቻይና በየሃገሮቻቸው ገንዘብ መገበያየት የሚችሉበትን ስምምነት መፈፀማቸውን ኢትዮጵያ ገልጻለች።
የገንዘብ ልውውጥ ስምምነት ትላንት መደረሱን የገለጹት የገብዘብ ሚንስትሩ አህመድ ሺዴ፣ በማዕከላዊ ባንኮች ንግግር ላይ በመመስረት ስምምነቱ እንደሚተገበር ጠቁመዋል፡፡
ስምመነቱ የተለያዩ ጠቀሜታዎች እንዳሉት የገለፁት የምጣኔ ኃብት ተንታኝ አቶ ክቡር ገና በበኩላቸው ከሁለቱ ሀገሮች አቅም እና የንግድ ልውውጥ ሚዛን አለመመጣጠን ጋራ በተገናኘ አነጻጽረው የቻይና ተጠቃሚነት ከፍ ሊል እንደሚችል አብራርተዋል፡፡ በመሆኑም፣ በልውውጥ የሚገኘውን ገንዘብ ኢትዮጵያ ለኢኮኖሚው ጠቃሚ በሆኑ ዘርፎች ላይ ማዋል እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡