ለአንድ ሳምንት ቆይታ ወደ ሕዋ የተጓዙት ባለሙያዎች፣ ለምን ለወራት ሳይመለሱ ቀሩ?
የዘጠኝ ቀናት ያህል ቆይታ ለማድረግ ‘ቦይንግ ስታርላይነር’ በተሰኘችው መንኮራኩር ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ/ም ወደ ሕዋው የመጠቁት የጠፈር ሳይንስ ባለሙያው ቤሪ ዊልሞር እና ሴቷ የጠፈር ባለሙያ ሱኒ ዊሊያምስ፣ መንኮራኩሯ እክል ስለገጠማት ቢያንስ ለስምንት ወራት ለመቆየት እንደሚገደዱ ታውቋል።
ባለሙያዎቹ በዓለም ዓቀፉ የሕዋ ጣቢያ ካሉና ምድርን ከለቀቁ ከረምረም ያሉ ባለሙያዎችን ተቀላቅለው መፍትሄ እስከሚገኝ ለመጠበቅ ተገደዋል።
መንኮራኮሯ የገጠማትን ችግር እና ባለሙያዎቹ በተራዘመው ቆይታቸው የሚያከናውኑትን ተግባራት እንዲሁም መንግስታዊ የሆነው የአሜሪካው የጠፈር ምርምርና አስተዳደር ማዕከል በምፃሩ ናሳ፣ የግል ኩባንያዎች መኮራኩርንና ሌሎችንም ሮኬቶች ወደ ሕዋ እንዲያመጥቁ የያዘውን ፕሮግራም በተመለከተ ባልደረባችን እንግዱ ወልዴ ሂዩስተን በሚገኘው የናሳ ጆንሰን የሕዋ ማዕከል፣ በተለይም በሕዋ ጨረርና የአየር ሁኔታ ጉዳዮች ከፍተኛ ባለሙያው ዶ/ር ጥላዬ ታደሰን አነጋግሮ ተከታዩን አጠናቅሯል።
የቦይንግ ስታርላይነር መንኮራኩር ዛሬ ወደ ምድር ለመመለስ በዝግጅት ላይ መሆኗ ታውቋል። የምትመለሰውም፣ እንደተከታተላችሁት፣ ለባለሙያዎች ደህንነት ሲባል ተጓዥ ሳይኖራት ባዶዋን እንደሆነም ታውቋል።