በአንድ ቀን 615 ነጥብ 7 ሚሊዮን ተክለናል ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከትናንት በስቲያ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መግለጫ፣ 29፡1 ሚሊዮን ዜጎች በ318፡4 ሄክታር ስፍራዎች ላይ ችግኞችን መትከላቸውን አመልክተዋል።
ባለፉት አምስት ዓመታት በተካሔደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ 32፡5 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውን የሚገልፀው የኢትዮጵያ መንግስት በዘንድሮው መርሃግብር ፣ቁጥሩን 40 ቢሊዮን ለማድረስ ማቀዱንም አስረድቷል።
ይሄንኑ ተከትሎም፣ የኢትዮጵያ የደን ሽፋን በ2011 ከነበረበት 17፡2 በመቶ፣ አሁን 23፡6 መድረሱን ገልጿል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ የሚበረታታ መሆኑን የሚቀበሉ አንዳንድ ወገኖች፣ ቁጥሩ ግን የተጋነነ ነው በማለት ጥርጣሪያቸውን ይገልፃሉ ።