የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ኩባንያ የኾነው አሚያ ፓወር፣ በኢትዮጵያ በ628 ሚሊዮን ዶላር የነፋስ ኀይል ለማመንጨት፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ ከመንግሥት ጋራ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
አሚያ ፓወር፥ በሶማሊ ክልል፣ በአይሻ – አንድ የነፋስ ኀይል ማመንጫ ጣቢያ፣ 300 ሜጋ ዋት ኃይል በማልማት ለ25 ዓመታት ለመንግሥት እንደሚያቀርብ፣ በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡
የግል ባለሀብቶች በኀይል ልማት ዘርፍ እንዲሰማሩ፣ ከስድስት ዓመት በፊት፣ የመንግሥት እና የግል አጋርነት ዐዋጅ ጸድቆ ሥራ ላይ መዋሉንና ይህም ኩባንያ በዐዋጁ መሠረት ወደ ሥራ መግባቱን፣ የመንግሥት የሥራ ሓላፊዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡