እስከ ኅልፈተ ሕይወት የሚያደርስ ጉዳት እያስከተለ ባለው ከፍተኛ የአካባቢ አየር ሙቀት ሳቢያ የሚመጣው የጤና ሁከት በሁለት እንደሚከፈል ለሞያዊ ትንታኔው የጋበዝናቸው እንግዳችን ዶክተር ነጋ ዓሊ ይናገራሉ።
በእንግሊዝኛው አጠራሩ Heat Stroke በመባል የሚታወቀው ሸንቋጭ የፀሐይ ሐሩር የሚያስከትለው የጤና ሁከት ዋና ዋና ምልክቶች ምንነት እና በተለይ ለሐሩር ተጋላጭ የኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ማንነትም አስረድተውናል።
ዶክተር ነጋ፣ ከዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው የሜሪላንድ ክፍለ ግዛቷ ራክቪል ከተማ፣ የሼዲ ግሮቭ የአድቬንቲስት የጤና ክብካቤ ክሊኒክ፣ በተላላፊ በሽታዎች እና በጽኑ ሕሙማን ልዩ ሕክምና ያገለግላሉ። ሞያዊ ማብራሪያቸውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።