- መግቢያ
ቢ.ጂ.አይ-ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የአልኮል እና ከአልኮል ነፃ የሆኑ መጠጥ አምራቾች ውስጥ ግንባር ቀደም እና በ53 የዓለማችን ሐገራት ውስጥ
በምርቶቹ የሚታወቀው የካስቴል ግሩፕ አካል ነው። ቢ.ጂ.አይ. ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥራትና ተወዳጅነት ያላቸውን ምርቶቹን ማለትም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፣ ካስቴል
ቢራ ፣ ሜታ ቢራ እና ስንቅ ማልትን በማምረት እና ለገበያ በማቀረብ ይታወቃል።
ቢ.ጂ.አይ. ኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካትና የበለጠ ተደራሽ ለመሆን የሚያስችሉትን ስራዎች እያከናወነ ይገኛል።
በዚሁ መሰረት ቢ.ጂ.አይ. ኢትዮጵያ ምርቶቹን ለማከፋፈል ፍላጎት ያላቸውን ግለሰብ እና ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱት ሁኔታዎች የሚያሟሉ ከሆነ አብሮ
ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት እንዲገልፁ ጥሪ ያቀርባል። - የስራው ሃላፊነት
አብሮን የሚሰራ አከፋፋይ የሚከተሉትን ሃላፊነቶች መከወን ይኖርበታል፡
- ለነባር እና አዳዲስ ደንበኞች ያልተቋረጠ የምርት ክፍፍል እና ደረጃውን የጠበቀ የደንበኞች አገልግሎት መስጠት።
- የድርጅቱን የሽያጭ እና የማስታወቂያ ስልቶች በአጥጋቢ ሁኔታ መከወን።
- የሽያጭ እና ሌሎች የግብይት መረጃዎችን እና ሰነዶችን በትክክለኛው ሁኔታ መዝግቦ መያዝ።
- የሽያጭ አፈጻጸም እና የገበያውን ግብረ መልስ በየጊዜው ሪፖርት ማቅረብ።
- የፍላጎት ማሳወቂያው ያካተታቸው የሽያጭ ዞኖች
አመልካቾች የፍላጎት ማሳወቂያቸውን ለሚከተሉት የሽያጭ ዞኖች ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። - አከፋፋዩ እንዲያሟላ የሚጠበቁ መስፈርቶች
ውጤታማ የቢ.ጂ.አይ. ኢትዮጵያ ምርቶች አከፋፋይ ለመሆን ቢያንስ የሚከተሉን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።
4.1. ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጥራት መለኪያዎች የሚያሟላ እና ቢያንስ የ5 ቀናት ሽያጭ ማስተናገድ የሚችል 400 ካሬ ላይ ያረፈ መጋዘን ያለው፣
- በብሎኬት የተሰራ መሆን አለበት፤
- በቂ አየር እና ብርሃን ሊኖረው ይገባል፤
- ንጹህ ወለል ፤ እንዲሁም ከወለሉ እስከ ጣሪያው ቢያንስስ 6 ሜትር ርዝመት ያለው፤
- ከዋና ገበያ በቅርብ ርቀት የሚገኝ እና ለከባድ የጭነት መኪናዎች እንቅስቃሴ በቂ ግቢ ያለው ሊህፕን ይገባል።
4.2. ከፋብሪካ ምርት ለማመላለስ የሚያስችሉ የከባድ ጭነት መኪናዎች እና ለደንበኞች በየበራቸው ለማድረስ የሚያስችሉ መካከለኛ የጭነት መኪናዎች
(ለምሳሌ፡ ISUZUs NPR) ያላቸው፣
4.3. የአከፋፋዩን የሽያጭ እና የአስተዳደራዊ ስራዎችን ለመከወን የሚያስችል የሰው ሀይል መመደብ የሚችል።
4.4. የተደራጀ ቢሮ እና ፈጣን ኢንተርኔት ያለው፤
4.5. ለሚያመለክቱት የገበያ ቦታዎች የጠለቀ ዕውቀትና ስለ ቢ.ጂ.አይ. ኢትዮጵያ ምርቶች የተለየ ፍላጎትት ያለው፤
4.6. ከዚህ ቀደም በአላቂ ዕቃዎች ጅምላ ሽያጭ ከፍተኛ ልምድ ያለው፤
- ወልዲያ
- ቆቦ
- ሎጊያ
- ደሎመና
- ጎሮ
- ጊንር
- ጂንካ
- ዲላ
- ያቤሎ
10.ነገሌ ቦረና - ሳውላ
- ሞያሌ
- ዱራሜ/ ሓላባ
- ኮንሶ
- ቋራ
- ጭልጋ
- ሳንጃ
- ወረታ
- ባህር ዳር
- ደብረ ማርቆስ
- ፍኖተ ሰላም
- ቻግኒ
- በቆጂ
- ዓዲግራት
- መሆኒ
- ሑመራ
- ዳንሻ
- አሶሳ
- ነጆ
- ጊምቢ
- አርጆ
- ቂልቱ ካራ
- ጉተን
- ደምቢ ዶሎ
- በደሌ
- ቦንጋ
- መቱ
- ሚዛን
- ቴፒ
- ዲማ
- ሸዋ ቤንች
- ጋምቤላ
- ጭሮ
- ሐረር
- ጅግጅጋ
- አዋሽ አርባ
- ሒርና
- አለማያ
ADDIS ABABA, ETHIOPIA
251 912 547896 | 251 912 547896 | BGIETHIOPIA.COM | BGIE.INFO@CASTEL-AFRIQUE.COM - የፍላጎት ማሳወቂያውን ለማስረከብ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
ፍቃደኝነቱ እና ብቃቱ ያላችሁ አመልካቾች አብሮ የመስራት ማመልከቻችሁን እና ከታች የተዘረዘሩትን ሰነዶች በግልጽ በሚታይ ኮፒ አካል በቢ.ጂ.አይ ዋና መስሪያ
ቤት በመቅረብ ወይም http://bgieoi.unaux.com/?i=1 ኦንላይን ፎርም ላይ በመሙላት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ
አርብ ግንቦት 23 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰአት በፊት ማመልከት ይችላሉ፡፡
5.1. ቴክኒካል ፕሮፖዛሉ ቢያንስ እነዚህን ማካተት አለበት:
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
- የግብር መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት
- የሁለት አመት የሂሳብ መዝገብ ሪፖርት እና የ2015 ዓም የታክስ ኪሊራንስ ሰርተፍኬት
- የስራ ማስኬጃ በቂ ካፒታል ያለው መሆኑን የሚያሳይ የሁለት አመት የባንክ እስቴትመንት ማቅረብ
- አከፋፋዩ የኃ.የተ.የግ.ማ ወይንም የአክስዮን መሃበር ከሆነ ስራ አስኪያጁ ድርጅቱን መወከል የሚያስችል የውክልና ወረቀት ማቅረብ ይኖርበታል
- የድርጅቱ የምስረታ ሰነዶች (ለ የኃ.የተ.የግ.ማ እና አ/ማ )
- የድርጅቱ አጭር መግለጫ፤ የንግድዎን ባህርይ ፤ ታሪክ ፤ የአገልግሎት ጥራት እና ብቃት የሚያሳይ የድርጅቱ መግለጫ።
- አመልካቹ መሰማራት የሚፈልግበትን የማከፋፈያ የገበያ ቦታዎችን የሚገልጽ ደብዳቤ
- ዋናው የስራ ቦታ: የሊዝ ማረጋገጫ ውል ወይም የንብረት ካርታ ኮፒ፤
- በአካባቢው ለረጅም ጊዜ ነዋሪ የሆነና በአካባቢው ማህበረሰብ መልካም ስም ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፤
- ማህበራዊ እና ህጋዊ ግዴታዎችን በአግባቡ እየተወጣ ያለና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ለጭነት መኪናዎቹ እና ለመጋዘኑ የባለቤትነት/ ሕጋዊ ውክልና ወይም የኪራይ ማረጋገጫ
- የስራ አስኪያጁ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ /መንጃ ፍቃድ/
- የመጠጥ ወይንም ለስላሳ መጠጦች/ምርቶችን የማከፋፈል ልምድ ያለው ይበረታታል፡፡
- በአካል የሚገቡ ማመልከቻዎች በሰም በታሸገ ፖስታ መቅረብ ያለበት ሲሆን ፖስታው ላይ የአመልካቹ ድርጅት ስምና ጉዳዩ በጉልህ ሊፃፍ ይገባል።
- በኦንላይን ፎርሙ የሚገቡ ማመልከቻዎች የሰነዱ አይነት በሚገልፁት መዘርዝሮች ውስጥ በትክክል ሊጫኑ ይገባል።
- የቢጂአይ ኢትዮጵያ ሃላፊነት
- ቢ.ጂ.አይ. ኢትዮጵያ የምርቶቻችንን ተደራሽነት ለማሳደግ እና ለማስፋፋት የውድድር ምህዳሮችን ፤ ሽያጮችን እና የንግድ ግብይትን በተመለከተ አስፈላጊውን ድጋፍ
ይሰጣል።
- ተጠያቂነትን በተመለከተ
- ይህ ማስታወቂያም ሆነ በውስጡ የያዛቸው ሐሳቦች ምንም አይነት ውል ወይም የሕግ ተጠያቂነትን በቢ.ጂ.አይ. ኢትዮጵያ ላይ አይፈጥሩም።
- ቢ.ጂ.አይ. ኢትዮጵያ ይሄንን ማመልከቻ በሙሉም ሆነ በከፊል የመቀየር ወይም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ። ማመልከቻው የሚዘጋበትን
ቀን ተሟልቶ ካልቀረበ ማመልከቻው ባዶ እንደሆነ ይቆጠራል ። - ቢ.ጂ.አይ. ኢትዮጵያ ማንኛውንም ማመልከቻ ለመቀበል ወይም መስፈርቱን ለማያሟሉ የፍላጎት ገላጮች ስራውን ለመስጠት አይገደድም ።
- መስፈርቱን የሚያሟሉ አመ?ካቾች ያቀረቡትን ማስረጃ ትክክለኛነት ቦታው ላይ ተገኝቶ ለማረጋገጥ በስልክ የምናገኛቸው ይሆናል።
- ይህ ጥሪ ለሁሉም ፍላጎቱ ላላቸው አመልካቾች ክፍት መሆኑን ልብ ይበሉ።
- ቢ.ጂ.አይ. ኢትዮጵያ የተሻለ መንገድ ካገኘ የንግድ መስፈርቶቹን የሚያሟላ ማንኛውንም አመልካች የመምረጥ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አብሮ ለመስራት ያለዎትን ተነሳሽነት እና አቅም በመጠቀም አብረን እንደምንሰራ ተስፋ እናደርጋለን።
The post የቢ.ጂ.አይ. ኢትዮጵያ ምርቶችን ለማከፋፈል የወጣ ማስታወቂያ appeared first on Capital Newspaper.