ዛሬ ሰኞ በተካሔደው የቦስተን ማራቶን፣ የ33 ዓመቱ ሲሳይ አፈትልኮ በመውጣት ግማሹን የማራቶን ርቀት በብቸኝነት ተቆጣጥሮ አሸንፏል።
ፀሐይ ከረር ስትል ፍጥነቱን ቢቀንስም፣ ሁለት ሰዓት ከስድስት ደቂቃ ከ17 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቋል። የገባበት ፍጥነት፣ በ128 ዓመት የውድድሩ ታሪክ ውስጥ 10ኛው ፈጣን ሰዓት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
በውድድሩ የፈጣን ሰዓት ክብረ ወሰን ባለቤት በመኾን የቦስተን ማራቶንን ያሸነነፈው ሲሳይ፣ ባለፈው ዓመት በቫሌንሺያ፣ ሁለት ሰዓት ከዜሮ ሁለት ደቂቃ ከዜሮ ዜሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት፣ ክብረ ወሰኑን ሰብሮ በመግባት አራተኛው ሆኗል።
ሲሳይ፣ የመጀመሪያውን ግማሽ ማይል 1:00:19 ሰዓት በመሮጥ፣ በዚህ ርቀት ባለክብረ ወሰን የነበረውን ጀፍሪ ሙታኢን ያስመዘገበውን ሰዓት በ99 ሰኮንዶች በመቅደም ሰብሯል፡፡
በዛሬ ውድድሩም፣ ራሱን ከሌሎች ነጥሎ በማውጣት ይህንኑ ብቃቱን አሳይቷል፡፡ በ41 ሰከንዶች የተቀደመው ኢትዮጵያዊ መሐመድ ዒሳ፣ ሲሳይን ተከትሎ ሁለተኛ ሲወጣ፣ ኬንያዊው ሻምፒዮን ኢቫንስ ቼቤት፣ አንደኛ ከወጣው በአንድ ደቂቃ ከአምስት ሰከንድ ርቆ ሦስተኛ ወጥቷል።
በሴቶች በተካሔደው የ2024 ቦስተን ማራቶን ደግሞ፣ ኬንያዊቷ ሄለን ኦቢሪ አሸናፊ ኾናለች፡፡
ኦቢሪ፣ የቦስተኑን ውድድር በሁለት ሰዓት ከ22 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ በማጠናቀቅ ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ አሸንፋለች፡፡
ሄሌን ኦቢሪ እ.ኤ.አ ከ2005 ጀምሮ፣ የቦስተን ማራቶንን አከታትላ በማሸነፍ የመጀመሪያዪቱ ሴት በመኾን ወሰነ ሬከርዷን አስጠብቃለች፡፡
ኢቢሳ ነገሰ ማምሻውን ከሲሳይ ለማ እና ከኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ጋራ አጠር ያለ ቆይታ አድርጓል።
ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።