አራቱ ጠፈርተኞች ‘ስፔስኤክስ’ በተባለችው የጠፈር መንኩራኩር አማካኝነት በስድስተኛ ወራቸው ነው ከዓለም አቀፉ የጠፈር ምርምር ጣቢያ ወደ ምድር የተመለሱት። በዩናይትድ ስቴትሱ የኤሮኖቲክስ እና የጠፈር አስተዳደር – ናሳ ተመራማሪዋ ጃስሚን ሞግቤሊ የተመራው የጠፈረተኞች ቡድን ከዴንማርክ፣ ከጃፓን እና ከሩሲያ የተውጣጡ ተመራማሪዎች ያሉበት ናቸው።
አራቱ ጠፈረተኞች 199 ቀናት ለወሰደው የጠፈር ምርምር ተልዕኳቸው ባለፈው የነሐሴ ወር ነበር ከምርምር ጣቢያው የገቡት። ተተኪዎቻቸው ባለፈው ሳምንት ከዓለም አቀፉ የጠፈር ምርምር ጣቢያ መድረቸው ተዘግቧል።
መንኩራኩራቸው ዛሬ ማክሰኞ ማለዳ ላይ ነው ከፍሎሪዳ ባሕረ ገብ መሬት አቅራቢያ ከሚገኘው የሜክሲኮ ባሕረ ሰላጤ ላይ አርፋለች።