የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ የባለአክስዮኖች 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አንቀጽ 367፤370፤371፤393፤እና394 እንዲሁም በባንኩ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 20 እና 21 መሠረት ቅዳሜ ታህሳስ 06 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮበአዲስ አበባ ሚሊኒየም አደራሽ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም ባለአክስዮኖች በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካይነት በተጠቀሰውቀን እና ቦታ በጉባኤው ላይ እንድትገኙ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡ስለባንኩ መግለጫ
- አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07
- የዋና ንግድ ምዝገባ ቁጥር KK/AA/3/005948/206
- የባንክ ሥራ ፍቃድ ቁጥር ለለበ/018/20112
- ይህ መግለጫ እስከ ተዘጋጀበት ድረስ የባንኩ ዋና ገንዘብ ብር 2,124,295,957.23
የ11ኛ መደበኛ የጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች - የጉባኤውን አጀንዳ ማጽደቅ፤
- እ.ኤ.አ የ2022/23 የአክሲዮን ዝውውሮችና፣ አዳዲስ አክሲዮኖች ሽያጭ ማሳወቅ፤
- እ.ኤ.አ የ2022/23 የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ማድመጥ፤
- እ.ኤ.አ የ2022/23 የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማድመጥ፤
- በተራ ቁጥር 3 ላይ በቀረበው የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ መወሰን፡፡
- በተራ ቁጥር 4 ላይ በቀረበው የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ላይ ተወያይቶ መወሰን፡፡
- እ.ኤ.አ የ2022/23 የተጣራ ትርፍ ድልድል እና አከፋፈል ላይ ተወያይቶ ውሳኔ መስጠት፡፡
- የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ዓመታዊ የስራ ዋጋ እና ወርሃዊ የአበል ክፍያ መወሰን፤
- የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ ሪፖርት ማዳመጥና ለቀጣዮቹ 3 ዓመታት የሚያገለግሉ የቦርድ አባላትን ምርጫ
ማካሄድ፡፡ - የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ ናቸው፡፡
ማሳሰቢያ፡- - በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክስዮኖች ይህ የጥሪ ማስታወቂያ ከወጣበት ጉባኤ ለመካሄድ ሁለት ቀን ሲቀረው
ማለትም እሰከ ታህሳስ 04 ቀን 2016 ቀን 10፡00 ሰዓት ድረስ ከኢትዮጵያ ሆቴል በስተጀርባ ናሽናል ታወር ከሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ
ቤት 9ኛ ፎቅ ፋይናንስና አካውንትስ መምሪያ አክሲዮን ክፍል በመገኘት የእንደራሴነት/የዉክልና ቅጽ በመሙላት ወይም ውል ለማዋዋል
ሥልጣን ካለው አካል በጉባኤው ላይ ለመገኘት እና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የተሰጠ የውክልና ማስረጃ ዋናውንና አንድ ቅጅ ይዞ
በመምጣት በጉባኤው ላይ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ - በጉባኤው ላይ በአካል የምትገኙ ባለአክስዮኖችም ሆናችሁ ወኪሎች የባለአክስዮኑን ኢትዮጵያዊነት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊነትን
የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፤ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን ፡፡ - በተጨማሪም የድርጅት ተወካዮች የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ወይም ተመሳሳይ የኃላፊነት ደረጃ ላይ ያሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ
ማስረጃ ወይም ድርጅቱን ወክለው እንዲገኙ የሚያረጋግጥ የተመዘገበ ቃለጉባኤ ወይም ውል ለማዋዋል ሥልጣን ካለው አካል የተሰጠ
የውክልና ሰነድ ይዘዉ መቅረብ ያለባቸው መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ
የዳይሬክተሮች ቦርድ