አንድ ወር ያስቆጠረው የእስራኤል ሐማስ ጦርነት፣ እጅግ ተጠናክሮ መቀጠሉንና ችግሩም ኾነ መፍትሔው በሁለቱም ወገኖች እጅ እንደኾነ፣ በእስራኤል እና በኢትዮጵያ የሚገኙ ነዋሪዎች እና ምሁራን ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ፡፡
በቴል አቪቭ ዩኒቨርሲቲ የሴማዊ ሥነ ቋንቋ ከፍተኛ መምህር ዶር. አንበሴ ተፈራ እና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ኮምዩኒኬሽን መምህር ዶር. ጀማል መሐመድ፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ
የችግሩም የመፍትሔውም አካል እንደኾነ ገልጸዋል፡፡ በደቡብ እስራኤል እና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የኾኑት ወሮ. ጸጋ ብሩክ እና አቶ አትክልት ተስፋዬም፣ ከወር በፊት በሐማስ ከተካሔደው ጥቃትም በኋላ፣ አሁንም በችግር ላይ እንደኾኑ አመልክተዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።