የጨረታ ቁጥር EH-2023-001
ኢንጀንደርሄልዝ አለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን በሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ባለስልጣን በምገባ ቁጥር 1233 የተመዘገበ በቤተሰብ ዕቅድ፣ የእናቶች ጤና እና ተያያዥ የተዋልዶ ጤና አገልግሎቶች ከጤና ሚኒስቴር ጋር በትብብር የሚሠራ ድርጅት ነው፡፡፡
ኢንጀንደርሄልዝ ሲገለገልባቸው የነበሩ ከታች የተዘረዘሩ አምስት ተሸከርካሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በድርጅቱ የአዋሽ ባንክ ሂሳብ ቁጥር ኢንጀንደርሄልዝ ኢንክ 01308254054900 በማስገባት እና የገቢ ደረሰኝ በመያዝ ከ22 ማዞርያ ወደ ብራስ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ወርቁ ህንጻ አካባቢ ከአበጋዝ ሆቴል ፊት ለፊት ከሚገኘው ቢሮ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 (አስራ አምስት ) ቀን ድረስ ክፍት ይሆናል፡፡ ማንኛውም ሰነድ የገዛ ተጫራች ከሀምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከታች በተጠቀሰው አድራሻ ንብረቶቹን መመልከት የሚችል ሲሆን ተጫራቾች የዋጋ ማቅራቢያቸውን በሰም በታሽግ ኢንቨሎፕ ድርጅቱ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ከሀምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰአት ድረስ በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ለሚጫረቱት ተሽከርካሪ መነሻ ዋጋ 20% በሲፒኦ ማሰያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሀምሌ 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልጽ ሕጋዊ መታወቂያ ወይም ሕጋዊ ውክልና እና የጨረታ ሰነድ ግዥ የተፈጸመበትን ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸል፡፡
ኢንጀንደርሄልዝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
አድራሻ
ከ22 ማዞርያ ወደ ብራስ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ወርቁ ህንጻ አካባቢ፤ አበጋዝ ሆ{ል ፊትለፊት
ስልክ ቁጥር 0116-63-08-33