የደቡብ ኮሪያ ህግ አውጭዎች ፣ ሀገሪቱን በወታደራዊ አመራር ውስጥ ለማድረግ በሞከሩት ፕሬዚደንት ዩን ሱክ ዮል ላይ ስልጣናቸውን ሊገፍ የሚችል ክስ መስርቶባቸዋል። ይህ ከፍተኛ እርምጃ ተፈጸሚ ይሆን ዘንድ በዳኞች መጽደቅ አለበት።
በዛሬው ዕለት በነበረው ድምጽ አሰጣጥ ስነ ስርዓት ላይ ፣ 12 ወግ አጥባቂ ህግ አውጭዎች ተቃዋሚ ኃይሎችን በመቀላቀል ፣ በአምስት አመት የስልጣን ዘመናቸው አጋማሽ ላይ በሚገኙት ዮን ላይ ስልጣናቸውን የሚገፍ ክስ እንዲመሰረት ወስነዋል ። ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንቱ በይፋ ከስልጣን መነሳት እንዳለባቸው እስኪወስን ድረስ የአሁኑ እርምጃ የዮንን ሥልጣን በጊዜያዊነት ያግዳል።
በጊዜያዊነት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀን ደክ ሱ የተጠባባቂ ፕሬዚደንትነት ኃላፊነቱን ይረከባሉ።
የድምጽ አሰጣጥ ስነ ስርዓቱ ከመጀመሩ ከደቂቃዎች በፊት ፣ ዩን የመጡነት ገዥው ህዝባዊ ጉልበት ፓርቲ ሂደቱን የተቃወመ ቢሆንም ፣ ካለፈው ሳምንቱ የሂደቱ ላይ አድማ በተጻራሪ አባላቱ በነጻነት ድምጻቸውን እንዲሰጡ ግን ፈቅዷል። በሚስጢር ከተሰጠው ድምጽ ጋር ተዳምሮ የውሳኔው ሚዛን ከዩን ተቃራኒ እንዲያጋድል አድርጓል። 204 ህግ አውጪዎች ህጉን በመደገፍ 85ቱ ደግሞ በመቃወም ድምጻቸውን እንደሰጡ የመጨረሻው ድምጽ አሰጣጥ ውጤት ያሳያል።
ከብሔራዊ ምክር ቤቱ ውጭ የተገኘ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ሕዝብ ደስታውን ሲገልጽ ታይቷል።
ዩን ደቡብ ኮሪያ በ1980ዎቹ ዴሞክራሲያዊት ሀገር ከሆነች ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓዊያኑ ጥር 3 ላይ በሀገሪቱ ወታደራዊ አስተዳደርን ተግባራዊ ለማድረግ ያወጁ የመጀመሪያ ሰው ሆነዋል። ይሁንና ህግ አውጪዎች አዋጁን በሰዓታት ውስጥ ቀልብሰውታል።
ዩን ስልጣናቸውን ለመግፈፍ ስለቀረባባቸው ክስ እስካሁን መልስ አልሰጡም።