በሚዙሪ ክፍለ ግዛት የሚገኙ መራጮች አሜሪካ ውስጥ ከሚገኙ ጥቅብ ሕጎች መካከል አንዱ የሆነውን የሚዙሪ ጽንስ የማቋረጥ መብት ክልከላ ሕግ ቀልብሰዋል፡፡
የመብት ተሟጋቾቹ ሰባት ክፍለ ግዛቶች ከተቀዳጇቸው ድሎች ይህ ድል አንደኛው ሆኗል፡፡ በፍሎሪዳ፣ ነብራስካ እና ደቡብ ዳኮታ ግን ተመሳሳይ የሕገ መንግሥት ማሻሻያዎችን ድል በመንሳት እገዳው በቦታው እንዲቀጥል አድርገዋል፡፡
ጽንስ የማቋረጥ መብቶች ማሻሻያዎቹ በአሪዞና፣ ኮሎራዶ፣ ሜሪላንድ እና ሞንታና አልፈዋል። የኔቫዳ መራጮችም ማሻሻያውን አጽድቀውታል፡፡ ተግባራዊ እንዲሆን ግን እኤአ በ2026 እንደገና እንዲያልፍ ማድረግ አለባቸው።
ሌላው በኒውዮርክ የታየው ድል “የእርግዝና ውጤት” ላይ የተመሰረተውን መድልዎ የሚከለክል ነው።
ፅንስ በማቋረጥ ሂደት ውስጥ አንዳንድ የመጀመሪያ ደረጃ ውጤቶች አሉ፡፡ እኤአ በ2022 የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚያስደንቅ ሁኔታ ሮ ቪ ዌድ የተባለውንና በሀገር አቀፍ ደረጃ ጽንስ ማቋረጥ የሚፈቅደውን ህገመንግሥታዊ መብት አስቀርቷል፡፡ እገዳው በሪፐብሊካኖች ቁጥጥር በሚገኙ በአብዛኛዎቹ ክፍለ ግዛቶች ስር ተግባራዊ እንዲሆኑ መንገዱን የሚጠርግ ነው፡፡
ሪፐብሊካን ዶናልድ ትረምፕ የፕሬዝዳንትነቱን ቦታ ባሸነፉበት በዚሁ ምርጫም ጉዳዩ እንደገና ተነስቷል። ትረምፕ ፅንስ በማቋረጥ ላይ ካለቸው ወጥነት የጎደለው አቋማቸው መካከል “ጉዳዩ ለክልሎች የተተወ ጉዳይ ነው” ብለው መናገራቸው ይጠቀሳል። ፕሬዝዳንቱ አሁንም በአስፈጻሚ ሥልጣናቸው በሚወስዷቸው እርምጃዎች በፅንስ ማቋረጥ ፖሊሲ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ፡፡
በዚህ መካከል ሚዙሪ በሁሉም የእርግዝና እርከኖች ፅንስ ማቋረጥ የሚከለክለው ህግ በድምጽ የሚሻርባት የመጀመሪያ ግዛት ትሆናለች፡፡ በግዛቲቱ ህግ አውጭዎች ጽንስ ማቋረጥ የሚቻልበትን የእርግዝና ጊዜን ብቻ እንዲያሻሽሉ የሚፈቅድ ነው፡፡ ትክክለኛው ጊዜ ባይታወቅም 21 ሳምንታት ተብሎ ይወሰዳል፡፡
እገዳው እና ሌሎች ገዳቢ ህጎች ግን ወዲያውኑ አይሰረዙም። ተሟጋቾች ከአዲሱ ማሻሻያ ጋር ሕጎችን እንዲሽሩ ፍርድ ቤቶችን መጠየቅ አለባቸው።
ሚዙሪ ለህገመግስታዊ ነጻነት የተባለ እንቅስቃሴ ቡድን አስተባባሪ በሰጡት መግለጫ “የሚዙሪ ሰዎች ዛሬ ታሪክ ሠርተው ግልጽ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ እርግዝናን በተመለከተ የሚደረጉ ውሳኔዎች ፅንስ ማቋረጥ፣ የወሊድ መቆጣጠሪያ እና የፅንስ መጨንገፍን ጨምሮ የግል እና የግል ውሳኔ ናቸው፡፡ ለፖለቲከኞች ሳይሆን ለታካሚዎችና ለቤተሰቦቻቸው ብቻ የተተወ መሆን አለበት” በማለት ተናግረዋል፡፡
ከ2,200 በሚበልጡ የክፍለ ግዛቱ መራጮች ላይ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት፣ ከሚዙሪ መራጮች ግማሽ ያህሉ ፅንስ ማቋረጥ በሁሉም ወይም በአብዛኛው ህጋዊ መሆን አለበት ብለዋል። ነገር ግን ፅንስ ማቋረጥ በሁሉም ጉዳዮች ሕገ-ወጥ መሆን አለበት ያሉት ከ 10 ውስጥ አንዱ ብቻ ናቸው ። በአብዛኛዎቹ ጉዳዮች ፅንስ ማስወረድ ሕገ-ወጥ መሆን እንዳለበት ከ10ሩ ውስጥ አራት የሚሆኑት ተናግረዋል ።
ድምጾች ከተሰጡ በኋላ በሦስት ግዛቶች ውስጥ እገዳዎች እንደነበሩ ይቆያሉ፡፡
ጽንስን ማቋረጥን የሚከለክለው ህግ ከተቀለበሰ በኋላ ጽንስ የማቋረጥ መብትን በመቃወም በምርጫው ያሸነፉ ፍሎሪዳ፣ ነብራስካ እና ደቡብ ዳኮታ የመጀመሪያዎቹ ግዛቶች ናቸው፡፡ አብዛኞቹ መራጮች የፍሎሪዳን ህገመንግስታዊ ማሻሻያውን ለማጽደቅ የሚጠይቀውን 60 ከመቶ ድምጽ ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡
በአሪዞና፣ አዲሱ ማሻሻያ ከ15 ሳምንታት በኋላ ፅንስ ማቋረጥ የሚከለክለውን የቀድሞ ህግ ይሽራል፡፡ ከ1900ዎቹ በፊት የነበረውን ገዳቢ ህግም ይተካል። በተመሳሳይ፣ የኮሎራዶ ማሻሻያ ፅንስ ለማስወረድ ለክፍለ ግዛቶች የገንዘብ ድጋፍ ተደራሽ ማድረግን ይፈቅዳል፡፡
ሮ ቪ ዌድ እኤአ በ 2022 የተቀለበሰ በመሆኑ 13 ግዛቶች ፅንስ ማቋረጥን በጥብቅ ያገዱ ሲሆን አራት ሌሎች ግዛቶች ደግሞ ከስድስት ሳምንታት በኋላ ፅንስ ማቋረጥን ከልክለዋል፡፡ ይህ ቢሆንም የፅንስ ማቋረጫ እንክብሎች አጠቃቀም እና የጉዞ ርዳታ በመጨመሩ ፅንስ ማቋረጥ በመጠኑ የተረጋጋ ሆኗል።
በዚህ ምርጫ ውስጥ ፅንስ ማቋረጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለብዙ መራጮች ቁልፍ ጉዳይ የነበረ ሲሆን የአሶሴይትድ ፕሬስ ቮት መረጃ እንደሚያሳየው፣ አንድ አራተኛ የሚሆኑት መራጮች እንደ ዋና ጉዳይ ቅድሚያ ሰጥተውታል፣ ግማሽ የሚጠጉትም አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል።