በትግራይ ክልል አለ ያሉት ችግር፣ በአንድ ፖለቲካ ፓርቲ ብቻ የሚፈታ አይደለም፤ ሲሉ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተናንት ጀነራል ጻድቃን ገብረ ትንሣኤ ተናገሩ።
በጊዜያዊ አስተዳደሩ በተዋቀረ አጥኚ ግብረ ኀይል አስተባባሪነት፣ የክልሉን ፖለቲካዊ አስተዳደር የሚዳስስ ውይይት በመቐለ ከተማ ተካሒዷል።
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ምሁራንና የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች በተሳተፉበት በዚኹ ውይይት፣ በክልሉ ያለው ችግር ምንጭ፣ ሕገ መንግሥቱን አክብሮ ያለመሥራት እንደኾነ፣ በመድረኩ በቀረበ ጥናት ላይ ተገልጿል፡፡
በመድረኩ ላይ አስተያየት የሰጡት የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ዐማኑኤል አሰፋ፣ ችግሮችን አብዝቶ መደርደር “ተስፋ መቁረጥ እንዳያመጣ” የሚል ስጋት አንጸባርቀዋል።
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።