ቤጂንግ በዛሬው ዕለት ይፋ ያደረገችው የመከላከያ በጀት ጭማሪ፡ ዩናይትድ ስቴትስን በመከተል በዓለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ወታደራዊ በጀቷን 1ነጥብ 6 ትሪሊዮን ዬን ወይም 222 ቢሊዮን ዶላር ያደርሰዋል። አሃዙ ባለፈው ዓመት ካደረገችው የበጀት ጭማሪ ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ተጠቁሟል።
ከራዳር ዕይታ ውጭ መሆን ከሚችሉ በራሪ ተዋጊዎች እና ዘመናዊ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚዎች፣ ይበልጥ እየተራቀቁ እስከመጡት የኒውክሊየር ጦር መሣሪያዎች ድረስ በወታደራዊ ቴክኖሎጂው ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው እመርታ፡ ብርቱ ሽኩቻ በሚታይበት የደቡብ ቻይና ባህር ‘የይገባኛል ጥያቄ’ ሳቢያ ቤጂንግ ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ታይዋን፣ ጃፓን እና ጎረቤቶቿ ጋር የገባችውን ውጥረት እያከረረው ነው።
ዛሬ በሀገሪቱ ምክር ቤት ዓመታዊ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ይፋ የተደረገው ይህ በጀት የገዥው የኮሚኒስት ፓርቲ ወታደራዊ ክንፍ፣ ለምርምር እና ልማት እንዲሁም የውጭ ጦር መሣሪያዎች ግዢ ከሚያውለው ጋር ተጠቃሎ የሚታሰብ ከፊል የበጀት ወጭ ነው ተብሏል። የቻይና የመከላከያ በጀት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2015 ከነበረው በእጥፍ ማደጉም ተመልክቷል።